...ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ፕሮፌሰርነቱን ለምኖና አላምኖ አንዳንዴም የጥቅምና የአሸማጋይነት ሚና ገብቶበት ማግኘት እየተለመደ ይመስላል። ስለዚህ ፕሮፌሰሮቹን የአዘቦት ሊቆችና ታላቅ ሊቆች ብለን መከፋፈል ግድ እያለ ነው። ታላቆቹን ሊቆች ማርሽ ቀያሪና የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት የሚችሉ ናቸው። ነገር ግን በየመስኩ ማርሽ ቀያሪ የሆኑ ብዙ ፕሮፌሰሮች አሉ ለማለት ይከብዳል።