ሚተራሊዮን
[by] በ አለማየሁ ዋሴ
153 Birr (Save 10%)
Price Out of Ethiopia: 25 USD
Book Weight: 300 g
In Stock
Book Description Overview
… የእኛ ሀገር የቱሪዝም ሥራ ነጥብ ላይ ያተኮረ (Spot Tourism) እንጅ መስመር ያለው (Route Based) ነው ለማለት ይቸግራል፡፡ የነጥብ ቱሪዝሙም ቢሆን ያሉንን ቅርሶች ከሚያኮስስ ድህነት ጋር መሣ ለመሣ እያሳየን፣ ከፊት የነበርን ከኋላ መቅረታችንን እያሳበቅን የምናስጎበኘው በመሆኑ ቱሪስቱን ከማስደነቅ ይልቅ አሁን ያለንበትን እያየ እንዲሳቀቅ የሚያደርግ ነው፡፡ በየትኛውም ዓለም ላይ የማይገኙ ቅርሶችን ጽዳት በጎደለው አካባቢ በልመናና በወከባ አጅበን አስጎብኝተን ገንዘብ ለማግኘት የምንጥር ጉዶች ነን፡፡ … ከዚህም በላይ ክዋኔን ያላካተተ፣ እየፈራረሰ ያለ ግንብና የቆመ ሃውልት በማሳየት ብቻ የተመሠረተ ነው፡፡ ምናልባት ከላሊበላ በስተቀር … ሕንፃዎቹና ሃውልቶቹ የተሠሩበት ጥበብና ቁስ ክዋኔ ሞዴል (simulation) ያካተተ አይደለም፡፡ በጥቅሉ ክዋኔ የሌለው በመሆኑ ቱሪስቱን የማያሳትፍ ከመሆኑም በላይ ቆይታውንም የተጣደፈ ያደርገዋል፡፡
Customer Reviews
ሚተራሊዮን
[by] በ አለማየሁ ዋሴ
153 Birr (Save 10%)
Price Out of Ethiopia: 25 USD
Book Weight: 300 g
In Stock